• "ልጄ 'ማሚ እኔ ይኼን ቆዳዬን አልወደምው፤ ቀዪሪልኝ' ሲለኝ የተሰማኝን ስሜት በቃል ለመግለፅ ይከብዳል። በጣም ነው የከፋኝ።" ወ/ሮ ጌጤ ነጋሽ
    Mar 26 2026
    ወ/ሮ ጌጤ ነጋሽ፤ በሀገር ቤት ጎሠኝነትን፣ በሀገረ አውስትራሊያ ዘረኝነትን እምቢኝ ያሉ፤ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በእጅጉ የኩራት ሞገስን የተላበሱ ናቸው። ልጃቸው ዕድሜው አምስት ዓመት ሊሞላ ደርሶ ሳለ የገጠመው የቀለም ልዩነት ያሳደረባቸውን ሥነ ልቦናዊ ሁከት እንደምን የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ፈውስ ሆኗቸው ከእነ ልጃቸው እንደተቋቋሙት ይናገራሉ። ያም አስባብ ሆኗቸው "አድዋና ሜልበርን" ያሏትን የስንኝ ቋጠሮ ያስደምጣሉ።
    Show more Show less
    23 mins
  • "ጠብን፣ መቀየምን ትፈራለች፤ ፍቅርን፣ ሰው ማክበርን ትወዳለች። በእምነቷም፣ በልጆቿም በትዳሯም ጠንካራ ነበረች።" የወ/ሮ ወርቅነሽ ባለቤት አቶ አብርሃም ተዘራ ገሠሠ
    Mar 26 2026
    ወ/ሮ ወርቅነሽ ጥላሁን ካሳ (ቤዛ) ለሶስት ዓመታት ከማኅፀን ካንሰር ጋር ያካሔዱት ፍልሚያ አክትሞ ከእዚህ ዓለም በሕልፈተ ሕይወት ተለይተዋል። ባለቤታቸው አቶ አብርሃም ተዘራ፣ የቤተሰባቸው ወዳጅ አቶ ፍቅሬ (ራያ) ረታ እና የንስሃ አባታቸው መልአከ ፅዮን ቀሲስ እንግዳ ችሩ፤ የሜልበርን መካነ ሰላም ልደታ ለማርያም ወገብርኤል አስተዳዳሪ፤ የወ/ሮ ወርቅነሽን የሕይወት ዘመን አንስተው፤ ጥልቅ ሐዘናቸውን በመግለፅ ይዘክራሉ። የወ/ሮ ወርቅነሽ ጥላሁን ካሳ (ቤዛ) የቀብር ሥነ ሥርዓት ቅዳሜ ማርች 28 ቀን 2026 / መጋቢት 19 ቀን 2018 በወረቢ ቤተ መቃብር Corner Cemetery Rd & Railway Avenue 10:00 am ይፈፀማል።
    Show more Show less
    17 mins
  • ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ‘በጣም ትልቅ ስጦታ ሰጠችኝ‘ አሉ
    Mar 25 2026
    የግሪንስ ፓርቲ አውስትራሊያ ያለ ፓርላማ ይሁንታ ወደ ጦርነት እንዳትገባ የሚደነግግ ሕግ እንዲኖራት ፓርቲያቸው ዳግም መጠየቁን አስታወቁ
    Show more Show less
    7 mins
  • ኢትዮጵያ በዓለም 5ኛዋ ግዙፍ አበባ ላኪ ሀገር ተባለች
    Mar 25 2026
    በኢትዮጵያ የዩናይድ ስቴትስ ኤምባሲ ኢትዮጵያውያን የንግድና ጉብኝት ቪዛ አመልካቾች እስከ 15 ሺህ ዶላር የሚደርስ የማስያዣ ገንዘብ እንዲያሲይዙ የሚጠይቀው አሠራር ከመጋቢት 24 ቀን 2018 ጀምሮ ግብር ላይ እንደሚውል አስታወቀ
    Show more Show less
    9 mins
  • "ቀደም ሲል የጦርነት ድምፅ ሰምተን አናውቅም። አሁን ግን ሕብረተሰቡን በጣም የረበሸና በተለይ የሕፃናት ሥነ ልቦና ላይ ጎጂ ሆኖ ነው ያለው።" ሰዓሊ ተሰማ ተምትሜ
    Mar 24 2026
    የዶሃ - ኳታር ነዋሪ ሰዓሊ ተሰማ ተምትሜ አሥራቴ፤ የእሥራኤል - ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን ጦርነት በእሳቸውና በቤተሰባቸው፣ እንዲሁም፤ በኳታር ነዋሪ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት ላይ ስላሳደረውና እያሳደረ ስላለው ተፅዕኖ አንስተው ያስረዳሉ።
    Show more Show less
    17 mins
  • "የጋሞ ሰርከስ ትምህርት ቤትንና ኢትዮ-ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ማዕከልን እንደግፍ" ኧኒ ዴቪ እና ማርታ ቦረና
    Mar 24 2026
    ኧን ዴቪ የFlying Fruit Fly Circus አርቲስቲክ ዳይሬክተርና ማርታ ቦረና የጋሞ ሰርከስ ትምህርት ቤትና የኢትዮ-ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ማዕከል ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል፤ ቅዳሜ ማርች 28 / መጋቢት 19 ስለሚካሔደው የድጋፍ እራት ፕሮግራምና የእገዛ ፋይዳዎች ይናገራሉ።
    Show more Show less
    17 mins
  • ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ ሰላጤን የባሕር መስመር እንድትከፍት የ48 ሰዓታት ዛቻ አዘል የጊዜ ገደብ ሰጡ
    Mar 23 2026
    አውስትራሊያ ለአንድ ወር ያህል የሚበቃ የነዳጅ፣ ናፍጣና የአውሮፕላን ነዳጅ ክምችት እንዳላት አስታወቀች።
    Show more Show less
    7 mins
  • "የሰርከስ ባለሙያ ሆኜ በእዚህ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኔ ዕድለኛ ነኝ" አርቲስት ሶስና ወጋየሁ
    Mar 23 2026
    ወ/ሮ ሶስና ወጋየሁ፤ የጋሞ ሰርከስ ትምህርት ቤት መሥራችና የኢትዮ - ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ዳይሬክተር፤ ከጋሞ ሰርከስ ትምህርት ቤት እስከ እንጦጦ ፓርክ እያስገነባችው ስላለው የሰርከስ ማዕከል ተልዕኮዎችን አንስታ ትናገራለች። የአውስትራሊያ ጉብኝት ዓላማዋንም አስመልክታ ቅዳሜ ማርች 28 / መጋቢት 19 በሚሊኒየም ሃውስ የማኅበረሰብ ማዕከል 296 Nicholson St, Seddon ተገኝታ ታስረዳለች።
    Show more Show less
    18 mins